የአቶ ተካልኝ ፈለቀ በዳሶ አጭር የሕይወት ታሪክ ------/////////////////////////////////////------------- አቶ ተካልኝ ፈለቀ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ወደ ማያልፈው ዓለም በእግዚአብሔር ፍቃድ ተጠርተው ቢሄዱም በእንግድነት በነበሩብት ዘመናቸው የሠሩትን የሕይወት ታሪካቸውን በዚህ መልክ አስፍረነዋል :- አቶ ተካልኝ ፈለቀ ከአባታቸው ከአቶ ፈለቀ በዶሶ እና ከወ/ሮ አስካላ ተሊላ በ1969 (በ1962 ዓ.ም) ተወለዱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወህዶ ቤተ-ክርስቲያን አስተምሮት ስራዓትና ደንብ ተኮትኩቶው አደጉ እድሜያቸው ለዘመናዊ ትምህርት ሲደርስ በተወዱበት አካባቢ በሚገኝ በአሰላ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከ1ኛ- 8ኛ ክፍል ሲከታተሉ ቆይተው በጥሩ ስነ-ምግባርና ውጤት በማስመዝገብ እና ለሌሎችም ተማሪዎች አርያ በመሆን ቀጣዩን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዝዋይ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በጥሩ ውጤት አጠናቀው ካላቸው ከፍተኛ ትምህርት ፍላጎት ቀጣይ ትምህርታቸውን ዩኒቨርሲቲ በመግባት የመጀመርያ ድግሪያቸውንና የማስተር ድግሪያቸውን በኬምስትሪ አግኝተው ከስመ ጥር ሰዎች አንዱ ሆነዋል:: ብዚህም በተማሩት ትምህርት ለ 16 ዓመታት በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በዓለም ጤና በደብረሲና በመምህርነት እና በርዕሰ መምህርነት በማገልገል ብዙ ተማዎችን ለሀገርና ለወገን ጠቃሚ ዜጎች እንዲሆኑ አድርገዋል :: እንዲሁም አጋንበር ህንጻታ ማርያም ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ በአገልግሎት በገንዘብ ያዢነት ህዝብን በማስተባበር በተጨማሪም በአላቸው የስዕል ችሎታ ለቤተ-ክርስቲያን የቅዱሳትን ስዕሎችን በመሳል የበረከት ሥራ ሰርተዋል:: ከዚያም የአሜርካን የውጪ እድል አግኝተው ከባለቤ- ታቸው ከወ/ሮ ወይንሼት እና ከሁለት ወንድ ልጆቻቸውና ከአንድ ሴት ልጃቸው ጋር በመሆን ወደ አሜሪካ መተው በፍሪያስ ታክሲ ካምፖኒ እንዲሁም በተለያየ የታክሲ ካምፖኒዎች በሹፌርነት ለ 12 ዓመታት በምስጉና በተሸላሚ ሠራተኝነት አገልግለዋል:: እንዲሁም በሚኖሩበት በላስቬጋስ ከተማ በማህበራዊ ህይወት ተግባቢና ለሰዎች ለችግርም ሆነ ለደስታቸው ደራሽና ርህሩህ አዛኝ ነበሩ :: በዚህ ሁኔታ ኑሮን ሲኖሩ ሳለ ባጋጠማቸው ህመም ከ09/2020 እስከ 09/25/24 ድረስ በህክምና ሲረዱ ቆይተው መስከረም/25//24 ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ወደ ማያልፈው ዓለም በሞት ተለይተውናል :: የወንድማችንን ነፍስ በቅዱሳን እቅፍ ያሳርፍልን ለቤተሰቡ መጽናናትን ይስጥልን !!! ከቤተሰቡ የተላለፈ መልክት -------/////////////////////////////--- አቶ ተካልኝ ባጋጠመው ህመም ወቅት በመጠየቅ አይዟችሁ ብርቱ በማለትና እስከዝችም ሰዓት አብራችሁን ላላችሁ በሐዘናችንም ለረዳችሁን ና ሀዘናችንን ለተካፈላችሁን ወገኖቻችን እግዚአብሔር ብድራችሁን ይክፈልልን ሁላችሁንም እናመሰግናለን !!! ወ/ስባት ለእግዜአብሔር !!!!
Visits: 35
This site is protected by reCAPTCHA and the
Google Privacy Policy and Terms of Service apply.
Service map data © OpenStreetMap contributors